Arts TVArts TV
← NewsSocial

የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት  ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀብር ስነ ስርዓት ዝርዝር መርሃ ግበር ይፋ ሆነ፡፡

Arts TV · ሜይ 3 2019

የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት  ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀብር ስነ ስርዓት ዝርዝር መርሃ ግበር ይፋ ሆነ፡፡

የቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት  ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የቀብር ስነ ስርዓት ዝርዝር መርሃ ግበር ይፋ ሆነ፡፡rnrnየቀድሞው ፕሬዝዳንት የቀብር ስነስርዓት የመንግስት ከፍተኛ ባላስልጣናት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በሚገኘው በጴጥሮስ-ወ-ፓውሎስ መካነ መቃብር እሁድ ሚያዝያ 27 ቀን 2011 ዓም ከቀኑ በ9:00 ስዓት ይፈፀማል።rnrnእስከ ግብዓተ መሬቱ ድረስ የሚከተሉት ስነስርዓቶች ይከናወናሉ።rnrnነገ ቅዳሜ ሚያዝያ 26 ቀን 2011 ዓም ከንጋቱ 11:55 ቤተሰቦችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት የአስከሬን አቀባበል ስነስርዓት ይካሄዳል።rnrnእሁድ ሚያዝያ 27 ቀን 2011 ዓም ከጧቱ 1:00 ስዓት ጀምሮ እስከ 5:30 ባለው ጊዜ በሆስፒታልና በመኖሪያ ቤታቸው የተለያየ ዝግጅት ይካሄዳል።rnrnከቀኑ 5:30 ጀምሮ ስስከ 8:00 ስዓት ድረስ አስከሬኑ በሚሊኒየም አዳራሽ ኦፌሴላዊ የአስከሬን አሸኛኘት ስነስርዓት ይደረግለታል።rnrnከ8:00 ስዓት ጀምሮ አስከሬኑ ከሚሊኒየም አዳራሽ ተነስቶ አዲስ አበባ ወደ ሚገኘው ጴጥሮስ-ወ-ፓውሎስ መካነ መቃብር እንዲደርስ ይደረጋል።rnrnበመካነ መቃብር ስፍራው የሚካሄዱ ዝግጀቶች እንደተጠናቀቁ የግብዓተ መሬቱ ስነስርዓት በ9:00 ስዓት ይፈፀማል።rnrn 

More in Social