Arts TVArts TV
← NewsSocial

ናይጀሪያ ደቡብ አፍሪካን አስጠነቀቀች፡፡

Arts TV · ሴፕቴ 3 2019

ናይጀሪያ ደቡብ አፍሪካን አስጠነቀቀች፡፡

ናይጀሪያ በደቡብ አፍሪካ ያሉ ዜጎቿ ላይ የሚደርሰው ጥቃት እንዲቆም አስጠነቀቀች፡፡rnrnአቡጃ ባወጣችው መግለጫ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካ ከተሞች የሚገኙ ዜጎቿን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ለመውሰድ መዘጋጀቷን ይፋ አድርጋለች፡፡rnrnየውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ጥላቻን የሚያራምዱ ደቡብ አፍሪካዊያን በናይጀሪያዊያን ላይ ያደረሱት ጥቃት መንግስትን በእጅጉ አስቆጥቷል፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የናይጀሪያው የፕሬዝዳንት ማማዱ ቡሀሪ እና  የደቡብ አፍሪካው አቻቸው ሲሪል ራፋሞሳ በመጭው ጥቅምት ተገናኝተው በጉዳዩ ዙሪያ ለመምከር ቀጠሮ ይዘዋል፡፡rnrnየናይጀሪያ መንግስት በዜጎቹ ላይ የደረሰውን ጥቃት ተቀባይነት የሌለው እና ወደ አላስፈላጊ ውዝግብ የሚያስገባ ብሎታል፡፡rnrnከዚሁ ጋር በተያያዘ የዛምቢያ መንግስትም ለደቡብ አፍሪካ መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እዲያስቆም ጥሪ አቅርቧል፡፡rnrnከዚህም ባለፈ ከዛምቢያ ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚገቡና የሚወጡ አሽከርካሪዎች ከመንግስት መመሪያ እስኪደርሳቸው ድረስ ጉዞ እንዲያቆሙ ትእዛዝ አስተላልፏል፡፡rnrnየደቡብ አፍሪካ መንግስት ሁኔታውን ለማስቆም በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም ነገሩ ቀላል እንዳልሆነለት መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Social