ታንዛኒያኒያውያን በርካታ ህፃናትን እንዲወልዱ ከመሪያቸው ጥሪ ቀረበላቸው፡፡rnrnበቅፅል ስማቸው ቡል ዶዘር በመባል የሚታወቁት የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የሀገራቸው ሴቶች ብዙ ልጆችን እንዲወልዱ ጠይቀዋል፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ማጉፉሊ ይህን ጥሪ ያቀረቡበትን ምክንያት ሲያብራሩ ብዙ የሰው ሀይል ያላት ሀገራ ጠንካራ ኢኮኖሚ የመገንባት አቅሟም በዚያው ልክ ከፍ ይላል የሚል ነው፡፡rnrnፕሬዝዳንቱ ከዓለማችን ቻይን እና ህንድን ከአፍሪካ አህጉር ደግሞ ናይጀሪያን ለአብነት በመጥቀስ በአግባቡ ከመሩት የሰው ሀብት ምን ያህል ጠቃሚ እንደሆነ አብራርቷል፡፡rnrnይሁን እንጂ ይህ ሀሳባቸው በተቃዋሚዎች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም ነው የተባለው፡፡ የተቃዋሚዎቹ መከራከሪያ ደግሞ የ55 ሚሊዮነን ህዝብ ባለቤት የሆነቸው ታንዛኒያ በዓለማችን ፈጣን የህዝብ እድገት ያላት በመሆኑ እንዲያውም መመጠን ያስፈልጋል የሚል ነው፡፡rnrnበአሁኑ ጊዜ የታንዛኒያ የህዝብ እድገት መጠን በየዓመቱ በአማካይ ከ6 እስከ 7 በመቶ ሲሆን በአንድ ቤተሰብ ከአምስት ያላነሱ ህፃናት ይገኛሉ፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ






