Arts TVArts TV
← NewsSocial

ዩጋንዳ እና ሪፓብሊክ ኮንጎ የሚያስተሳስራቸውን መንገድ በጋራ ለመገንባት ተስማሙ፡፡

Arts TV · ኖቬም 12 2019

ዩጋንዳ እና ሪፓብሊክ ኮንጎ የሚያስተሳስራቸውን መንገድ በጋራ ለመገንባት ተስማሙ፡፡

ዩጋንዳ እና ሪፓብሊክ ኮንጎ በንግድ የሚያስተሳስራቸውን መንገድ በጋራ ለመገንባት ተስማሙ፡፡rnrnየኮንጎው ፕሬዝዳንት ፊሊክስ ሺሲኬንዲ ሰሞኑን ወደ ካምፓላ ተጉዘው ከዩጋንዳው አቻቸው ዩዌሪ  ሙሴቬኒ ጋር በመንገድ ግንባታው ዙሪያ ተመካክረዋል፡፡rnrnአሶሼትድ ፕሬስ እንደዘገበው ሁለቱን ሀገራ የሚያገናኘው መንገድ 1 ሺህ 200 ኪሎ ሜትር ይረዝማል፡፡rnrnዩጋንዳ ከሪፓብሊክ ኮንጎ ጋር የንግድ ትብብሯን ለማጠናከር ይህን ፕሮጀክት የምትሰራው በቅርቡ ከሩዋንዳ ጋር የነበራት ግንኙነት መቋረጡን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡rnrnበሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ መጠን ከግማሽ ሚሊዮን የማይበልጥ መሆኑን ያወሱት መሪዎቹ ከመንገዱ ግንባታ በኋላ ፈጣን እድገት እንደሚያመጣ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡rnrnየዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ይህን በማድረጋቸን መልካም የንግድ ትስስር በመፍጠር የጋራ ተጠቃሚ እንሆናለን ብለዋል፡፡rnrnየሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ፣ የመሰረተ ልማት እና የፋይናንስ ሚኒስትሮች በቅርቡ ተገናኝተው በግንባታው ዝርዝር ጉዳዩችን ዙሪያ ይወያያሉ ነው የተባለው፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Social