ኢትዮጵያ የእውቅና ሰርተፍኬት ተበረከተላትrnrnየአሜሪካ ናሽናል አክርዲቴሽን ቦርድ በመባል የሚታወቀው የጥራት መመዘኛ ተቋም የኢትዮጵያ የምግብና የመድኅኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የአውቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል፡፡rnrnየተበረከተው ሰርተፍኬት የመድኅኒት ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ እና የኮንዶም ጥራት ምርመራ ላቦራቶሪ በISO1725 ሁለተኛ ዙር ኦዲት በማድረግ መስፈርቶችን ሁሉ በመሟላታቸው ሲሆን የእውቅና ሰርተፊኬት እ.ኤ.አ. እስከ መያዚያ 2021 የሚቆይ እንደሆነ ተነግሯል፡፡rnየጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን ለዚህ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉትን የመስሪያ ቤቱን አመራሮችና ሰራተኞች በጤና ሚኒስቴር ስም አመስግነዋል፡፡rnበሌሎች ዘርፎችም የተጀመሩትን የጥራት ማረጋገጥ ስራዎችን ተጠናከረው እንደሚቀጥሉ ዶክተር አሚር አማን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡






