Arts TVArts TV
← NewsEconomy

ከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡

Arts TV · ሜይ 7 2019

ከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙንrnrnየገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡rnሚኒስቴሩ በተያዘዉ በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት በገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ በድምሩ 37 ሚሊዮን 488 ሺህ ,463.1 ብር የሚገመት ማዕድናት በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡rnበገቢ ኮንትሮባንድ 19 ሚለዮን ,445 ሺህ ,983.10 ብር እና በወጪ ኮንትሮባንድ 18 ሚሊዮን ,42 ሺህ ,480 ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ማዕድናት በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች መያዝ ችሏል፡፡rnበቁጥጥር ስር ከዋሉት ማዕድናት መካከል 19 ሚሊዮን 166 ሺህ 863.1 ብር የሚገመተው ብር፣ 11 ሚሊዮን 321 ሺህ ,600 ብር የሚገመተው ሌሎች ማዕድናት እና 7 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው ወርቅ ናቸው፡፡rnሀገራችን ከወርቅ የወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ በኮንትሮባድ እና ሌሎች ችግሮች ምክንያት መቀነሱን ሰሞኑን የተገለጸ ሲሆን ፤ ከአምስት ዓመታት በፊት ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ከወርቅ ስታገኝ የነበረ ቢሆንም ባለፈው ዓመት ከወርቅ የወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ 30 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ብቻ ሆንዋል ፡፡

More in Economy