ኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡rnrnየገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በህዝብ ተወካች ምክር ቤት ቀርበዉ የሚኒስቴሩን የአስር ወራት አፈጻጸም ሪፖረት ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ ሀገሪቱ ከዓለም አቀፍ ፋይናንስ ተቋማትና ከተለያዩ መንግስታት በብድርና እርዳታ 5.7 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት አቅዳ በአስር ወራት ዉስጥ ግን የ4.7ቢሊዩን ዶላር ድጋፍ እንዳገኘች ተናግረዋል፡፡rnrnበበጀት አመቱ ላይ መንግስት የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ እንዲኖር ጥብቅ የፊሲካል ፖሊሲ ተግባራዊ ማደረጉን እና የመንግሥት ወጪ በገቢው እንዲሸፈን ተደረጓል፡፡rnrnሀገሪቱ ከወጪ ንግድ 2.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የተጠቀሰ ሲሆን፤ከ2010 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው ገቢ ሲነጻጸር በ187.1 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ አሳይቶል፡፡rnrnእንደ ገንዘብ ሚነስቴር ገለፃ በ10 ወራት ዉስጥ 174 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር አጠቃላይ የፌዴራል መንግስት የተጣራ ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን 251 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር ደግሞ ወጪ መሆኑ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡rnrnአገሪቱ ከገጠማት የውጭ ምንዛሪ እጥረት አኳያ የውጭ ዕዳ ክፍያ ጫና ለማቃለል እና በቀጣይ ዕዳ የመክፈል አቅምን ለማጠናከር ከቻይና የፋይናንስ ተቋማት ጋር ድርድሮችን በማድረግ የወለድ መጠን ቅነሳ፣ የእፎይታ እና የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘም ተደረጓል፡፡rnrn rnrn
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
ኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
Arts TV · ጁን 6 2019

More in Economy
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyበደሴና ድሬዳዋ አካባቢዎች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ሺሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሜይ 3 2019

