የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡rnrnሚኒስቴሩ ይህንን የገለጸዉ የቆዳው ዘርፍ የሚመራበት ፍኖተ ካርታን አስመልክቶ በተካሄደ ዉይይት ላይ ነዉ፡፡rnrnፍኖተ-ካርታው በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣በኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣በቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት፣ በኢትዮጵያ ቆዳ ኢንዱስትሪዎች ማህበር እና በኢንተርፕራይዝ ፓርትነር የተዘጋጀ ነዉ፡፡rnየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረየስ በዉይይቱ ወቅት እንደገለጹት ኢትዮጵያ ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቷ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለምታደርገው መዋቅራዊ ሽግግር ትልቅ እርምጃ ነዉ ብለዋል፡፡rnrnየቆዳው ዘርፍ የሚመራበት ፍኖተ ካርታን አስመልክቶ በተካሄደ ዉይይትም አገራችን ከፍተኛ የእንሰሳት ሃብት እንዳላት የገልፁት አቶ ተካ ይህም የቆዳን ኢንዱስትሪ ወደፊት ለማስወንጨፍ መልካም አጋጣሚ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡rnrnየቆዳን ኢንዱስትሪ ልማትን ለማሳካት የግብርና ልማት እና የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂያችን እርስ በእርስ ሊመጋገቡ ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ፤ሁለቱ ሴክተሮች ተመጋግበውና ተናበው መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ጠቁመዋል፡፡rnrnሌላው በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦጋለ ፈለቀ የዚህ ፍኖተ-ካርታ መዘጋጀት ንዑስ ዘርፉን ለማሳደግ አዎንታዊ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡rnrnበሌላ በኩል ከ12 ያላነሱ ቆዳ ፋብሪካዎች በአቅም ዕጦትና በዕዳ መዘጋታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ መንግሥት ተግባራዊ ሲያደርገው የቆየው ፖሊሲ ከስድስት ዓመታት በላይ የሆነውና እሴት የተጨመረበት ብሎም ያለቀለት ቆዳ ወደ ውጭ እንዲላክ የሚያስገድድ ነው፡፡rnrnይህ ፖሊሲ በከፊል ያለቀለትና ከጥሬ ቆዳ ደረጃ ጥቂት ማሻሻያ የተደረገበት ምርት ወደ ውጭ እንዳይላክ ለማገድ፣ የ150 በመቶ የወጪ ንግድ ታክስ ማወጁ ኢንዱስትሪውን በተለይም የአገር ውስጥ ፋብሪካዎችን ለአደጋ እንዳጋለጠ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት፡፡rnrn rnrn
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
Arts TV · ሜይ 7 2019

More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyበደሴና ድሬዳዋ አካባቢዎች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ሺሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሜይ 3 2019

