Arts TVArts TV
← NewsEconomy

በኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡

Arts TV · ሜይ 10 2019

በኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡

በኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡rnrnይህ የተባለዉ የገቢዎች ሚኒስቴር  ኮንትሮባንድን ለመከላከል ከፍትህ አካላት ጋር በአዳማ  የዉይይት መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነዉ፡፡rnrnበመድረኩ ኮንትሮባንድ በየቦታው ኬላዎችን በማደራጀት ብቻ የሚፈታ ባለመሆኑ ኮንትሮባንድን በመያዝ፣ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የሚያውሉ፣ ምርምራ የሚያደርጉ እና ውሳኔ የሚሰጡ አካላት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባልም ብለዋል፡፡rnrnከችግሩ አሳሳቢነት አንፃር ጠንካራ የህግ ማቀፍ ሊኖር እንደሚገባም ተነግሯል፡፡ የህግ ማቀፎቹ የጉምሩክ ኮሚሽን እርምጃ መወሰድ የሚያስችለው ስልጣን የሚያጎናፅፉት መሆን አለባቸውም ተብሏል፡፡rnrnኮንትሮባንድን በሚያሳልፉ አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበትና የተሻለ የሰሩ እውቅና የሚሰጥበት አሰራር መዘርጋት ያስፈልጋልrnrnግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች በስፋት ሊሰሩ ይገባል የተባለ ሲሆን፤በአስፈፃሚ አካላት መካከል የሚታዩ የቅንጅት ችግሮች መፈታት አለባቸውም ተብሏል፡፡rnrnየጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ፤ኮንትሮባንድ የሚያስከትለውን ችግር ለመከላከል የፍትህ አካላት የተባበረ ስራ የሚያስፈልገው እንደሆነ ውይይቱን በከፈቱበት ወቅት ተናግረዋል፡፡rnrnበኮንትሮባንድ ንግድ የሚሳተፉ አካላት ላይ በቀጣይ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ ከፍትህ አካላት ጋር አንድ አቋም መያዝ ያስፈልጋል፡፡ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት መፍትሄው ላይ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡rnየኦሮሚያ ክ/መ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ደሳ ቡልቻ በበኩላቸው የፍትህ አካላት ህጋዊ አሰራርን ተከትሎ በቅንጅት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡ በጋራ ከሰራን ችግሩን በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍታት ይቻላል ነው ያሉት፡፡rnበአዳማ ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ዳኞች፣ አቃቤያን ህጎች እና በፍትህ ስርዓት ውስጥ ድርሻ ያላቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

More in Economy