በደሴና ድሬዳዋ አካባቢዎች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ሺሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡rnrnሚኒስቴሩ የያዝኳቸዉ እቃዎች በድምሩ ከ1,073,021 ብር በላይ የሚገመቱ ናቸዉ ብሏል፡፡rnrnከነዚህ ዉስጥ ግምታዊ ዋጋው 572,481 ብር የሚደርስ ኮንትሮባድ ሲጋራና ምስር ወደ ድሬዳዋ ከተማ ለማስገባት ሲሞከር የተያዘ ሲሆን፤ ኮንትሮባንዲስቶቹ ተኩስ በመክፈት የኮንትሮባድ ዕቃዎቹን ለማሳለፍ ሙከራ አድርገዉም ነበር ተብሏል፡፡rnrnበተመሳሳይ መስመር 350 ሺህ ብር የሚጠጋ እርጥብ ጫት በህገ-ወጥ መንገድ ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር በጉምሩክ ሰራተኞችና በመከላከያ ሰራዊት የጋራ ጥረት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡rnrnግምታዊ ዋጋው 316,200 የሆነ የምግብ ዘይት በኤፍኤስ አር ተሽከርካሪ በአማራ ክልል በጉባ ላፍቶ ወረዳ ሀራ ተብሎ የሚጠራ ቦታ በክልሉ ፖሊስ አባላት የተያዘዉም በዚህ ሳምንት ነዉ፡፡rnrnሸዋሮቢት አካባቢ በሀሰተኛ ደረሰኝ 34,340 ብር የሚገመት ሽቶ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ እና ደሴ ከተማ ውስጥም 719 ስቴካ ሺሻ መያዛቸዉንም ሰምተናል፡፡rnrnምንጭ ፤-ገቢዎች ሚኒስቴር
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
በደሴና ድሬዳዋ አካባቢዎች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎችና ሺሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
Arts TV · ሜይ 3 2019

More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019

