Arts TVArts TV
← NewsSocial

13ኛዉ አዲስ ፊልም ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል ቅዳሜና እሁድ የተለያዩ ፊልሞችን በማሳየት ይቀጥላል፡፡

Arts TV · ሜይ 3 2019

13ኛዉ አዲስ ፊልም ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል ቅዳሜና እሁድ የተለያዩ ፊልሞችን በማሳየት ይቀጥላል፡፡

13ኛዉ አዲስ ፊልም ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል ቅዳሜና እሁድ የተለያዩ ፊልሞችን በማሳየት ይቀጥላል፡፡rnrnበሳምንቱ መጀመሪያ የተከፈተዉ 13ኛዉ አዲስ ፊልም ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል ከ500 የዓለማችን ፊልሞች ዉስጥ 60ዎችን በመመረጥ በተለያዩ ቦታዎች ለፊልም አድናቂያንና ባለሞያዎች እያሳየ ነዉ፡፡rnrnከ60 የተመረጡ ፊልሞች ዉስጥ  24ቱ የኢትዮጵያ ፊልሞች ሲሆኑ፤ከነዚህ ዉስጥ 10 ስሩ የአጭር አጭር የሚባሉ ከ1 ደቂቃ አስከ 5 ደቂቃ የሚፈጁ ፊልሞች  መሆናቸዉን የአዲስ ፊልም ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል አስተባባሪ ቤዛዊት ዳምጠዉ ለአርትስ  ቲቪ ተናግራለች ፡፡rnrnለፊልም ባለሞያዎች ስራቸዉን ማሳያ ቦታ እድል የሚፈጥረዉና ከአለም የፊልም ባለሞያዎች ልምድ ለመቅሰም መድረክ የሆነዉ  ፌስቲቫሉ ዘንድሮም እንደ እቅዱ የተለያዩ ፊልሞችን በማሳየትና የፊልም ጥበብ ማሳደግ ላይ ያተኮሩ ወርክሾፖችን እያካሄደ መሆኑንም ከፊልሙ ፊስቲቫል አስተባባሪ ሰምተናል ፡፡rnrnበፊስቲቫሉም የፊልም ገበያ  በዓለም አቀፍና ሀገርዉስጥ፤የፊልም ታሪክ ነገራና ዝግጅት ሳቢነት፤አለምአቀፍ ኢንቨስቲጌቲቭ ፊልሞችን እንዴት መስራት ይቻላልና በኢንዱስትሪ ዉስጥ የሴቶች ሚናና የሚደርስባቸዉ ተጽእኖ እንዲሁም አጫጭር ፊልሞችን እንዴት  ለገበያ ማዋል ይቻላል የሚሉ ጉዳዩች   ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ዉይይት እየተደረገባቸዉ ነዉ፡፡rnrnፊልሞቹ በሀገር ፍቅር ቲያትር  በቫምዳስ ኢንተርቴመንት በብሄራዊ   የጣልያን ባህል ማዕከል ፤በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ  በብሄራዊ ቤተመጻህፍትና  ወመዘክር  ኤጀንሲ እና በሀገር ፍቅር እየታዩ ሲሆን፤ ቅዳሜና እሁድ ከሚታዩ ፊልሞች መካከል ቁራኛዬ በጣሊያን ባህል ማዕከል ቅዳሜ 12 ሰዓት  እንደሚታይም ከአዘጋጆቹ አርትስ ማወቅ ችሏል፡፡rnrn rnrn rnrn 

More in Social