1 ሺህ 77 የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወሰነ።rnrnየአዲስ አበባ ግብር ከፋይ የሆኑ እና ጉዳያቸው በፖሊስ እና በአቃቤ ህግ ተይዞ የነበሩ 1 ሺህ 77 ነጋዴዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወሰነ።rnrnየከተማ አስተዳደሩ የአዲስ አበባ ግብር ከፋይ የሆኑ ክሳቸው እንዲቋረጥና ፍርድ የተሰጠባቸው በምህረት እንዲለቀቁ ለፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ነዉ ክሳቸዉ የተቋረጠዉrnrnመዝገቦች እጅግ አነስተኛ የገንዘብ መጠን የያዙ ሆነው ያለ ደረሰኝ እና ከዋጋ በታች ግብይት የተከናወነባቸው፣ ደረሰኝ ሳይዙ ዲኪላራይሶን ሳይኖራቸው የተለያዩ ዕቃዎች በንግድ ሱቃቸው የተገኘባቸው፣ የባለስልጣኑን ስራ በማሰናከል እና ከሽያጭ መመዝገቢያ መሳርያ አድራሻ ጋር የተፈፀሙ ጥፋቶች በመሆናቸው እነዚህ ወንጀሎች ከአፈፃፀማቸው ፣ ከያዙት የገንዘብ መጠን አነስተኛ መሆን እንዲሁም ከተያዘው የታክስ ሪፎርም እና ከግለሰቦቹ የኢኮኖሚ አቅም አንፃር በምርመራ እና በፍ/ቤት ደረጃ ያሉ በሙሉ እንዲቋረጡ ቢደረጉ በመንግስት እና በህዝብ ጥቅም ላይ የሚያደርሱት ጉዳት ዝቅተኛ በመሆኑ ክሳቸው ተቋርጦ ወደ ስራ ቢገቡ የሚያበረክቱትን አስተዋፅዖ ከግምት ውስጥ በማስገባት ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወስኗል፡፡rnrnከመርካቶ የታክስ ሪፎርም አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ያደረጉት ኢ/ር ታከለ ኡማ መንግስት የንግዱን ማህበረሰብ ችግር ለመፍታት የሚሄደውን ርቀት ያህል ግብር ከፋይ ነጋዴውም የሚገባውን ግብር በወቅቱ በመክፈል ኃላፊነቱ እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡rnrn<strong> </strong>
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
1 ሺህ 77 የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ ተወሰነ።
Arts TV · ኤፕሪ 11 2019

More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019

