ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከፍትህ አካላት ጋር እየተወያዩ ነዉ፡፡rnrnጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመላዉ ሀገሪቱ ከተዉጣጡ ከ3 ሺህ ባለይ የአቃቤ ህግ ጠበቆችና የፍትህ ዘርፍ አመራሮች ጋር በፍትህ ስርዓቱ ለዉጥና የማሻሻያ ስራዎች ላይ ነዉ እየተወያዩ ያሉት፡፡rnrnጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍትሕ ዘርፍ ባለሞያዎች ውይይት መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ባለፈው አንድ ዓመት በዘርፉ የተካሄዱ የሕግ ማሻሻያዎች መሠረታቸውን በተቋማት ላይ ትኩረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል።rnrnበተለይም አቅምን የመገንባትና የመንግሥት ኃላፊዎችን ጨምሮ በሕግ የበላይነት የሚያምን ማኅበረሰብ የመፍጠርን አስፈላጊነት አሥምረውበታል።rnrnምንጭ፤- ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት






