ጉምሩክ ባላወጣው ጨረታ አታሎ የጨረታ ማስከበሪያ ለመቀበል የሞከረው ግለሰብ ተያዘrnrnነዋሪነቱ አዲስ አበባ የሆነው ይህ ግለሰብ ነጋዴዎችን አነጋግሮ በጉምሩክ ለጨረታ የቀረበ የግንባታ ብረት እንዳለ በማስመሰል አታሎ ገንዘብ ሊቀበል ሲል ጅግጅጋ ላይ ተይዟል።rnrnበጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የስራ ሃላፊዎች ስም የጨረታ ኮሚቴ ነኝ በማለት ለጨረታ ማስከበሪያ በሚል የሀሰት ማሳመኛ 690 ሺህ ብር ሊቀበል ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል።rnግለሰቡ ነጋዴዎችን ለማታለል የሞከረው ለጨረታ የቀረበ 2 ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ኪ.ግ የግንባታ ብረት በመኖሩ በአነስተኛ ዋጋ አሸናፊ ትሆናላችሁ በማለት ነው።rnጥርጣሬ ያደረባቸው ነጋዴዎችም ወደ ጅግጅጋ ጉምሩክ በማምራት ለማጣራት ባደረጉት ጥረት ግለሰቡ ሊያዝ ችሏል።rnግለሰቡ ከአዲስ አበባ እስከ ጅግጅጋ ኔትወርክ በመዘርጋት ካልተያዙ ሌሎች ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን ነው የማታለል እና የማጭበርበር ድርጊት ሲፈፀም የተደረሰበት።rnየጉምሩክ ኮሚሽን ህብረተሰቡ ከአጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቅና በተቋማት ስም ክፍያ ሲጠየቅ ከመክፈሉ አስቀድሞ ማረጋገጥ እንዳለበት ጥሪውን አስተላልፏል።
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
ጉምሩክ ባላወጣው ጨረታ አታሎ የጨረታ ማስከበሪያ ለመቀበል የሞከረው ግለሰብ ተያዘ
Arts TV · ኤፕሪ 8 2019

More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019

