Arts TVArts TV
← NewsEconomy

ጃፓን እና ቻይና ጉርብትናችንን ማጠናከሩ ይበጀናል እያሉ ነው፡፡

Arts TV · ኤፕሪ 15 2019

ጃፓን እና ቻይና ጉርብትናችንን ማጠናከሩ ይበጀናል እያሉ ነው፡፡

ጃፓን እና ቻይና ጉርብትናችንን ማጠናከሩ ይበጀናል እያሉ ነው፡፡rnrnዲያዎዩ በተባለችው በሁለቱ ሀገራ ድንበር በምትገኘው ደሴት ለዓመታት ሲወዛገቡ የኖሩት ጃፓን እና ቻይና ጉርብትናቸውን ለመልካም ነገር በማዋል የኢኮኖሚ ትስስራቸውን ለማጠናከር  ቃል ገብተዋል፡፡rnrnየቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ የሁለቱ ሀገራት መልካም ግንኙነት አሁን   ወደቀደመው በታ ተመልሷል ብለዋል፡፡rnrnሮይተርስ እንደዘገበው ቶኪዮእና ቤጂንግ ስድስት ወሳኝ በሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎች በጋራ ለመስራ ተስማምተዋል፡፡rnrnበቴክኖሎጂ በሀይል ቁጠባ እና አጠቃቀም፣ አንዲሁም በአካባቢ ጥበቃ እና በሌሎችም መስኮች አብረው ለመስራት ነው የተስማሙት፡፡rnrnየጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታሮ ኮኖ በበኩላቸው ሁለቱ የዓለማችን የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤቶች ይህን መሰል ስምምነት ማድረጋቸው ለዓለም ኢኮኖሚ የሚተርፍ ስራ ይሰራሉ ብለዋል፡፡rnrnሁለቱ ሀገራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቤጂንግ ባዘጋጀችው የጃፓንና የቻይና የወጣቶች ዓመታዊ የወዳጂነት ስነ ስርዓት ላይ ተገናኝተው ነው ስምምነቶቹን ያደረጉት፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙrnrn rnrn rnrn 

More in Economy