የፌደራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ በስራ ፈጠራ፣ የዋሉ ብድሮችንና ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በላይ የቆዩ የማምረቻና መሸጫ ሼዶችን በማስመለስ ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት ተገለፀ፡፡rnይህ የተጠቆመው የኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኤጀንሲው ባደረገው የመስክ ምልከታ ወቅት ነው፡፡rnቋሚ ኮሚቴዉ የኤጀንሲውን የስራ እንቅስቃሴ ቃኝቷል፤ በቁልፍ ተግባራት አፈጻፀምና ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያም የኤጀንሲውን የስራ ሀላፊዎችና ሰራተኞችን አወያይቷል፡፡rnበውይይቱም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘነበ ኩሞ በስራ ዕድል ፈጠራ በኩል በ6 ወራት ውስጥ ያለው አፈጻጸም 80% መድረሱን በከተማ የምግብ ዋስትና በ11 ከተሞች ከ445 ሺህ በላይ ዜጎች በዘላቂ ድጋፍና በሴፍቲኔት ፕሮግራም በአካባቢ ልማት ላይ በመሳተፍ ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡rnአመላመላቸውም በህብረተሰቡ በቂ ግምገማ ተደረጎ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡rnrnየአለም ባንክ ሂደቱን በጥሩ አፈጻጸም የገመገመ በመሆኑ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ሀላፊው የተናገሩት፡፡rnይህ እንዳለ ሆኖ የፋይናንስ አቅርቦት፣ የመስሪያ ቦታ፣ ብድር እና ሼዶችን በማስመለስ ሂደት ላይ የሚስተዋሉትን ችግሮች በእጥረት አንስተዋል፡፡rnየቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው በስራ ዕድል ፈጠራ ላይ እየታየ ያለው መቀዛቀዝ እና የማምረቻና የመሸጫ ሼዶችን በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ለምን ማስመለስ እንዳልተቻለ የጠየቁ ሲሆን፤ የስራ እድል ፈጠራው የተቀዛቀዘው በአገሪቱ አንዳንድ ቦታዎች በተከሰተው አለመረጋጋት ምክንያት መሆኑን፣ ለስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚዎች የሚሰጡ የማምረቻና የመሸጫ ሼዶች ለ5 አመታት ቢሆንም 10 እና ከዚያም በላይ አመታት ተጠቅመው ያልመለሱ አካላት መኖራቸው ተጠቁሞ በቀጣይ እነዚህን አካላት በመለየት የማስመለስ ስራ እንደሚሰራ ነው የኤጀንሲው የስራ ሃላፊዎቹ ምላሽ የሰጡት፡፡rnየቋሚ ኮሚቴው አባላት የኤጀንሲውን የለውጥና የመልካም አስተዳደር፣ የሴቶችጉዳይ፣ የውስጥ ኦዲት፣ የሂሳብና የንብረት አስተዳደር ክፍሎችን የስራ እንቅስቃሴ ተዟዙረው ተመልክተዋል፡፡rnየኤጀንውን ሰራተኞች ባወያዩበት ወቅትም በአገሪቱ አንዳንድ ቦታዎች ያለው አለመረጋጋት ስራቸውን ከቦታ ቦታ ተዘዋውረው ለመስራት ስጋት እንዳሳደረባቸው፣ የሚከፈላቸው የቀን አበልም የወቅቱን የኑሮ ደረጃ ያላገናዘበና የቢሮ አጥረትም ጭምር እንዳለባቸው ሰራተኞች ለቋሚ ኮሚቴ አባላት ተናግረዋል፡፡rnrn
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
የፌደራል የከተሞች የስራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ አላግባብ የተያዙ ማምረቻ ቦታዎችን ማስመለስ አለበት ተባለ፡፡
Arts TV · ኤፕሪ 16 2019

More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019

