የጅቡቲ-ገላፊ እና የታጁራ-በልሆ መንገዶች ግንባታ እየተፋጠነ ነውrnrnየጅቡቲ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሞሃመድ አብዱልካድር የጅቡቲ-ገላፊ እና የታጁራ-በልሆ መንገዶች ግንባታን አስመልክቶ ከተቋቋመው የአገሪቱ የቴክኒክ ኮሚቴ ጋር ውይይት አድርገዋል።rnrnበውይይቱ ለአሽከርካሪዎች አስቸጋሪ መንገድ የሆነውን የዲኪል-ጋላፊ መንገድ እንዲሁም የታጁራ-በልሆ መንገድ ግንባታን አስመልክቶ ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን በጥናቶቹ መሰረት የዲኪል-ገላፊ መንገድ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጨረታ በማውጣት ወደ ስራ የሚገባበት መንገድ ተጠቁሟል፡፡rnrnየትራንስፖርት ሚኒስትሩ ሞሃመድ አብዱልካድር እንዳሉት የመንገዶቹ ግንባታ መጠናቀቅ የአሽከርካሪዎች ደህንነት ከመጠበቅ ባሻገር የኢትዮጵያንና የጅቡቲን ብሎም የቀጠናውን የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተራክቦ ከፍ ወዳለ ደረጃ እንደሚያሳድገው ገልጸዋል፡፡rnrnበኢንቨስትመንት ጉዳዮች የአገሪቱ ፕሬዚዳንት አማካሪ ፋሃሚ አል ሃግ ፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሩ የቴክኒክ ጉዳዮች አማካሪ አህመድ አብዶ አሊ እና ሌሎች ሃላፊዎችም በስብሰባው ተገኝተዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።rnrnየትራንስፖርት ሚኒስትሩ አክለውም ቀሪው የታጁራ-በልሆ መንገድ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ገልጸው ለመንገዶቹ ግንባታ የገንዘብ እገዛ ያደረጉትን የሳዑዲ-አረቢያ እና የጃፓን መንግስታት አመስግነዋል፡፡rnrnበ15ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ ወቅት የመንገዶቹ ግንባታ በአፋጣኝ መጠናቀቅ የሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የሁለቱ አገራት ከፍተኛ ኃላፊዎች መምከራቸውና አቅጣጫዎች መቀመጣቸው የሚታወስ ሲሆን ጅቡቲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በኩል ክትትሎች እየተደረጉ መሆኑን መረዳት ተችሏል፡፡rnrn rnrn rnrn rnrn
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
የጅቡቲ-ገላፊ እና የታጁራ-በልሆ መንገዶች ግንባታ እየተፋጠነ ነው
Arts TV · ኤፕሪ 23 2019
More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019

