የኢትዮ-ሩስያ የስነ-ህይወታዊ አካላት የምርምር ማዕከል በኢትዮጵያ ሊቋቋም ነው፡፡rnየኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስት ዶ/ር ኢንጂ ጌታሁን መኩሪያ አዲስ ከተሾሙት በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢቭጀኒ ተረኪህን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡rnሚኒስትሩ የኢትዮጵያ እና የሩስያ መንግስታት የጋራ ኮሚሽን የኢትዮጵያ በኩል ሰብሳቢ በመሆናቸው የጋራ ኮሚሽኑ ስብሰባ በሚካሄድበት ቀንና በሚቀርቡ አጀንዳዎች ዙርያ ተነጋግረዋል፡፡rnየኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለህክምናና ለሃይል መጠቀም እንዲቻል በተቀመጠው ፍኖታ ካርታ ትግበራ ዙርያም መክረዋል፡፡rnየሩስያ የሳይንስ አካዳሚ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የኢትዮ-ሩስያ የስነ-ህይወታዊ አካላት የምርምር ማዕከል ለማቋቋም እቅድ ተይዟል፡፡rnጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተነጋግረው በሚያስቀምጡት አቅጣጫ መሰረት ወደ ትግበራ ይገባል፡፡rnከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዳገኘነዉ መረጃ የሩስያ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በማዕድን ፍለጋ መስክ ( በወርቅና ታንታለም) መሰማራት በሚችሉበት መንግድ ላይም ተወያተዋል፡፡





