Arts TVArts TV
← NewsEconomy

የአዲስ አበባን የታክሲ አገልግሎት ዘመናዊ የሚደርግ ዛይራይድ የተሰኘ የስልክ መተግበሪያ በድጋሚ ስራ መጀመሩን  ዛይቴክ አይቲ ሶሊውሽን አክሲዮን ማህበር ይፋ አደረገ

Arts TV · ማርች 14 2019

<strong>የአዲስ አበባን የታክሲ አገልግሎት ዘመናዊ የሚደርግ ዛይራይድ የተሰኘ የስልክ መተግበሪያ በድጋሚ ስራ መጀመሩን  ዛይቴክ አይቲ ሶሊውሽን አክሲዮን ማህበር ይፋ አደረገ፡፡</strong>rnrnየድርጀቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የሜትር ታክሲ እጥረት መኖሩን ተናግረው፤ አዲሱ የስልክ መተግበሪያ ያለአግባብ የሚጠየቁ ክፍያዎችን ከማስቀረት እና ከደህንነት አንጻር ተመራጭ ነው ብለዋል፡፡rnrnዛይራድ የስልክ መተግበሪያ በተጋጋሚ አዳዲስ ማሻሻያዎች የተደረጉለት ሲሆን በአነስተኛ የኔትወርክ አቅም ጭምር እንዲሰራ ተደርጓል ያሉት የድርጅቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ አቶ በረከት ባይሳ መተግበሪያው ለአጠቃቀም ቀላል መሆኑን ተናግረዋል፡፡rnrnየድርጅቱ የቢዝነስ አማካሪ አቶ ያሬድ ሃይለመሰቀል  በበኩላቸው ቴክኖሎጂው በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን ግዙፍ ኢኮኖሚ ያንቀሳቅሳል ነው ያሉት ፡፡rnrnዛይራይድ በአሁኑ ሰዓት 40 ሺ ደንበኞች ያሉት ሲሆን ከ20ሺ ሆቴሎች እና ከ18 በላይ ተቋማት ጋር በኮርፖሬት ይሰራል መባሉንም ሰምተናል፡፡rnrn&nbsp;

More in Economy