የባህርዳር ጤና ጣቢያ የቤት ለቤት ተመላላሽ ህክምና መስጠት መጀመሩ ተገለፀ፡፡rnጤና ጣቢያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሞደልነት ተመርጦ ለነዋሪዎቹ የቤት ለቤት ህክምና መስጠት መጀመሩን የጤና ጣቢያው ጊዜያዊ ተወካይ አቶ ተመስገን ደሌ ገልጸዋል፡፡rnrnበስሩ ካሉት አራት ቀበሌዎች በተጨማሪ ለአጎራባችና ከገጠር ቀበሌ ለሚመጡትም አገልጋይ እንደሆነ የጤና ሚኒስቴር አስነብቧል፡፡rnrnጤና ጣቢያው በእናቶችና ህፃናት ጤና፣ተላላፊ የሆኑና ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከልና ወቅት ጠብቀው የሚከሰቱ እንደ ወባ እና አተት የመሳሰሉ በሽታዎችን ቀድሞ በመቆጣጠር በኩል የቤት ለቤት ህክምናው ጠንካራ አቅም እየሆነ ነው ብለዋል።rnrn






