Arts TVArts TV
← NewsEconomy

የምግብ ዘይት በማምረት የሚታወቀው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የማሌዥያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ሊጀምር ነው

Arts TV · ኤፕሪ 23 2019

የምግብ ዘይት በማምረት የሚታወቀው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የማሌዥያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ሊጀምር ነውrnrn rnrnኩባንያው በኢትዮጵያ የምግብ ዘይት ምርት ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየቱን ተከትሎ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ለኩባንያው ሀላፊዎች በዘርፉ ባለው የኢንቬስትመንት እድል ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።rnrnበኢትዮጵያ ያለው የምግብ ዘይት ፍላጎት ከፍተኛ ቢሆንም 90 በመቶ የሚደርሰው ምርት ከውጭ አገራት በግዢ የሚገባ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ፈትለወርቅ በከተማም ሆነ በገጠር የህዝቡ የኑሮ ደረጃ በተሻሻለ ቁጥር የሸማቹ የምግብ ዘይት ፍላጎትና ምርጫ ከፍ ስለሚል በዘርፉ መሰማራት አዋጭ ነው ብለዋል።rnrnከውጭ አገራት የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለሚያመርቱ ኢንቬስተሮች አገሪቱ ጠንካራ የታሪፍ ጥበቃ እንደምታደርግ ሚንስትሯ አብራርተዋል፡፡rnrnየኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፎድ ሀይል በበኩላቸው በኢትዮጵያ ምቹ የኢንቬስትመንት እድሎች በመኖራቸው በምግብ ዘይት ዘርፍ መዋዕለ ንዋያችንን በስራ ላይ ለማዋል  ፍላጎት አለን ብለዋል።rnrnኩባንያው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ የምርት ስራውን እንደሚጀምርና ለ1 ሺህ 500 ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር በውይይቱ ላይ ተገልጿል።rnrnመረጃውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አግኝተነዋል።rnrn rnrn rnrn rnrn

More in Economy