ዋሽንግተን በግብጽ መከላከያ ተቋም ተቆጥታለች፡፡rnrnየግብፅ መከላከያ ሀይል በሀገሪቱ ባሉት የኢኮኖሚ ተቋማት የበዛ ጣልቃ ገብነት አለው የሚሉ የሪፓብሊካን እና የዲሞክራት ፓርቲ አባላት በሁኔታው ቅር መሰኘታቸውን ተናግረዋል፡፡rnrnየዲፕሎማቲክ መንጮች ተናገሩ ብሎ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው የፓርቲ አባላቱ የግብፅ መከላከያ ሁሉንም የኢኮኖሚ ዘርፎች ስለተቆጣጠረ የውጭ ኢንቨስተሮች ለኪሳራ እየተዳረጉ ነው ብለዋል፡፡rnrnግብፅ ውስጥ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የመከላከያ ሚኒስቴር በራሱ ቁጥጥር ስር ስላደረጋቸው የአሜሪካን ጨምሮ በርካታ የምእራባዊያን ኢንቨስተሮች በቢሊዮን ዶላር የሚገመት ኪሳራ ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡rnrnከአሁን ቀደም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው ሪፖርት የፕሬዝዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ መንግስት ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ አጀንዳዎቹን እንደገና መፈተሸ አለበት የሚል ሀሳብ አንፀባርቋል፡፡rnrnእንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2017 አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) በግብፅ የግሉ ዘርፍ በመዳከሙ እና የመከላከያው ጣልቃ ገብነት በማየሉ ስራ አጥነት እና የኢኮኖሚ እድገር ማሽቆልቆል እየተስፋፋ ነው ማለቱ የሚታወስ ነው፡፡rnrnበሀገሪቱ የሚገኙ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በተደጋጋሚ የኢኮኖሚ ፖሊሲውን ሲተቹ ይደመጣሉ ምን እንኳን ሰሚ ባያገኙም ይላል ዘገባው፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
ዋሽንግተን በግብጽ መከላከያ ተቋም ተቆጥታለች፡፡
Arts TV · ማርች 20 2019

More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019

