ኮፊ አረቢካ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተፈላጊነቱ እያደገ ነው ተባለ።rnrn rnrnበቻይናውያን ዘንድ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መጥቷል የተባለው ይኸው የኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ በሃገሪቱ በተካሄደ ዓለም ዓቀፍ ልዩ የቡና ትርኢት ቀርቧል።rnrn rnrnኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ይኸው አውደትርዒቱ ከመጋቢት 2 እስከ 8 ቀን 2011 ዓ.ም በቻይና ፑኤር ከተማ ተካሂዷል። እንደ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ገለፃ በትርዒቱ ኢትዮጵያ ያላትን የተፈጥሮ ቡና ልዩ ጣዕምና ጥራት እንዲሁም ብዝሃነት ለቻይና ህዝብ አስታዋውቃበታለች።rnrnኮፊ አረቢካ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ በቻይና ገበያ ተመራጭ መሆኑና በቻይናውያን ዘንድ ተፈላጊነቱ እያደገ መምጣቱም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።rnrn rnrnእንደ ኢትዮጵያ ያሉ ጥሬ ቡና የሚልኩ አገራት እሴት በመጨመር ቡና ለውጭ ገበያ ማቅረብ የሚያስቸሉበት ልምድም በአውደትርዒቱ ቀርቧል።rnrnከትርኢቱ ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ልዑክ ከፑኤር ከተማ ከፍተኛ ሃላፊዎችና የዩና ግዛት ዓለም አቀፍ የቡና ገበያ ቢሮ ተወካዮች ጋር በዘርፉ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።rnrnበፕሮግራሙ ላይ ቡና በማቀነባበር፣ በማልማት፣ በማምረት፣ በመሸጥና ተያያዥ ዘርፎች የተሰማሩ ከአንድ ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።rnrn
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
ኮፊ አረቢካ በመባል የሚታወቀው የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተፈላጊነቱ እያደገ ነው ተባለ
Arts TV · ማርች 18 2019

More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019