ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ቀጣና ስምምምነትን ለአፍሪካ ህብረት አቀረበችrnኢትዮጵያ በቅርቡ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በኩል ያጸደቀችውን የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ለአፍራካ ህብረት ገቢ አድርጋለች።rnrnበፕሮግራሙ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማህማት፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዋና አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ አገራት ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ ተገኝተዋል።rnrnየህብረቱ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት በዚሁ ወቅት እንዳሉት የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና የኢንዱስትሪ እና የተቋማትን ተወዳዳሪነት በማሳደግ በአህጉሩ ያሉ የገበያ እድሎችን አሟጦ ለመጠቀምና ሃብቶችን በአስፈላጊ አካባቢዎች እንዲገኙ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል።rnrnየ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዋና አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ በበኩላቸው ውሳኔው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጠንካራ ቀጣናዊ ትስስር እንዲኖርና ነጻ የሰዎችና የሃሰብ ዝውውር እንዲስፋፋ ካላቸው ራዕይ ጋር የሚጣጣም መሆኑን ገልጸዋል።rnrnየአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ስምምነት በአፍሪካውያን መካከል ያለውን ንግድ እንደሚያሳድገው፤ በቀጣናዊ የንግድ ማህበረሰቦች መካከል ብሎም በአህጉር ደረጃ የበለጠ ትስስር እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።rnrnስምምነቱ ከዓለም የንግድ ድርጅት ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ በአፍሪካ ትልቁ የንግድ ስምምነት ይሆናል።rnrnመረጃው የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ነውrnrn
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ የንግድ ቀጣና ስምምምነትን ለአፍሪካ ህብረት አቀረበች
Arts TV · ኤፕሪ 11 2019
More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019

