Arts TVArts TV
← NewsEconomy

ኢትዮጵያ ቡናን እሴት ጨምራ በመላክ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ 80 በመቶ ለማሳደግ እየሰራሁ ነዉ አለች፡፡

Arts TV · ኤፕሪ 8 2019

ኢትዮጵያ ቡናን እሴት ጨምራ በመላክ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ 80 በመቶ ለማሳደግ እየሰራሁ ነዉ አለች፡፡rnቴክኖሎጂን በመጠቀምና ቡናን እሴት ጨምሮ ወደ ውጭ በመላክ ኢትያዮጵያ ሀገራዊ የቡና ምርት ግብይት ላይ እሴት ለመጨመር የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ምክክር መድረክ በጅማ ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተካሄዷል።rnየምክክር መድረኩ በጅማ ከተማ የተገነባውን የኢንዱስትሪ ፓርክ በመጠቀም በአካባቢው የሚገኘው ቡና ላይ እሴት በመጨመር ለአለም ገበያ ማቅረብ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ነው።rnየኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ  ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ለዘመናት ሌሎች ሀገሮች የሀገራችንን ቡና እሴት በመጨመር ሲያገኙት የነበረውን ገቢ ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስቀረት ይሰራል ብለዋል።rnቡናን በጆንያ ወደ ውጭ ከመላክ የዘለለ ስራ አልተሰራም ያሉት ሚኒስትሩ፤ የቡና ምርት ላይ እሴት በመጨመርና በኤሌክትሮኒክስ ግብይት ስርዓት ውስጥ በማስገባት ኢትዮጵያ የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ የሚያስችል ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን  ተናግረዋል፡፡rnrn 

More in Economy