ኢትዮጵያ በ72 ኛው የጤና አለም አቀፍ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነዉ፡፡rnrnየጤና ሚኒስትሩ ዶክተር አሚር አማን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንደገለፁት የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጄኔቫ ስዊዘርላንድ እየተካሄደ ባለው 72ተኛው የጤና አለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ኢትዮጵያ ሁለት አዳዲስ ለውሳኔ የሚቀርቡ ሀሳቦችን ታቀርባለች፡፡rnrnኢትጵያ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ሁለት ጎን ለጎን የሚካሄዱ ስብሰባዎችን በማዘጋጀት የምትመራ እንደሆነም ተነግሯል፡፡rnrnየልዑካኑ ቡድኑ ከሌሎች ሀገራት ጋር የልምድ ልውውጥ እና አዳዲስ ትብብሮችን ለመፍጠር ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር ውይይት እንደሚያደርግም ዶክተር አሚር አማን አስታዉቀዋል፡፡rnrn






