Arts TVArts TV
← NewsSocial

ኢትዮጵያና ቻይና ግብርናን ጨምሮ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ያላቸዉን ግንኙነት አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ገለጹ፡፡

Arts TV · ሜይ 28 2019

ኢትዮጵያና ቻይና ግብርናን ጨምሮ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ያላቸዉን ግንኙነት አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያና ቻይና ግብርናን ጨምሮ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ያላቸዉን ግንኙነት አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ገለጹ፡፡rnrnየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ  ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ ከቻይና የግብርናና የገጠር ልማት ምክትል ሚኒስትር ዶ/ር ቹ ዶንጁ ጋር በጋራ ትብብርን በማጠንከር ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡rnrnኢትዮጵያያና ቻይና ግብርናን ጨምሮ በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ምሳሌ የሚሆን ጠንካራ ትብብር እንዳላቸው ዶ/ር ማርቆስ በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።rnrnየኢትዮጵያ የግብርናው ዘርፍ አሁንም በርካታ ተግዳሮቶች ያሉበት መሆኑን ጠቅሰው ቻይና ያላትን የካበተ ልምድ ለኢትዮጵያ እንደታካፍልም ጠይቀዋል።rnrnበተለይም በገበያ ትስስር፣ በግብርና ቴክኖሎጂ፣ በግብርና ፈጠራና መሰል ዘርፎች ኢትዮጵያ ልምድ ለመቅሰም ትፈልጋለች ብለዋል።rnrnየቻይና የግብርናና የገጠር ልማት ምክትል ሚኒስትር ዶ/ር ቹ ዶንጁ በበኩላቸው በሁለቱ አገራት በኩል ባለው ግንኙነት ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።rnrnሚኒስትር ዴኤታው ያቀረቧቸውን ድጋፎች ተግባራዊ እንዲሆኑ ግፊት እንደሚያደርጉም አስታውቀዋል።rnrnምክትል ሚኒስትሩ ለመንግስታቱ ድርጅት የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ዳይሬክተር ጄኔራልነት እየተወዳደሩ መሆናቸውን በመግለጽ ቢመረጡ የሚያከናውኗቸውን ዋና ዋና እቅዶችም ለሚኒስትር ዴኤታው አብራርተውላቸዋል።rnrn 

More in Social