Arts TVArts TV
← NewsSocial

ኢትዮጵያና ቻይና የመሬት ምልከታና ብሮድካስት ሳተላይት በጋራ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

Arts TV · ሜይ 28 2019

ኢትዮጵያና ቻይና የመሬት ምልከታና ብሮድካስት ሳተላይት በጋራ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ኢትዮጵያና ቻይና የመሬት ምልከታና ብሮድካስት ሳተላይት በጋራ ለመገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡rnrnስምምነቱን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲቲዩት ዳይሬክትር ዶ/ር ሰለሞን በላይ እና የቻይና ሮኬት ካምፓኒ ምክትል ፕሬዝዳንት ሃን ቺንፒንግ ፈርመውታል።rnrnግንባታው በኢትዮጵያና ቻይና ባለሙያዎች ትብብር የሚከናወን ሲሆን 50 በመቶ የሀገር ውስጥ እሴት እንዲጠቀም ይደረጋል ነው የተባለው።rnrnበግንባታው የሚሳተፉ ኢትዮጵውያን ከቻይና የቴክኖሎጂ ልምዱን ይወስዳሉ ተብሏል። ተጠቃሚ መለየት፣ ማስተባበር፣ ፍላጎትና ቦታ መረጣ የመሳሰሉት ተግባራት ሰኔ ወር ላይ ይጀመራሉ።rnrnየአሁኑ የሳተላይት ግንባታ ስምምነት ሳተላይትን የስራ እድል መፍጠሪያ እና ሃብት ማመንጫ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ ነው።rnrnአንደ ኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ኢንስቲትዩት ገለፃ  በሁለቱ ሀገራት ትብብር የተሰራችው የመጀመሪያዋ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ህዳር 2012 ወደ ህዋ እንደምትልክም ይጠበቃል፡፡

More in Social