Arts TVArts TV
← NewsEconomy

አዲስ የተቋቋመው የጉሙሩክ ፖሊስ ስራ ጀመረ

Arts TV · ኤፕሪ 23 2019

አዲስ የተቋቋመው የጉሙሩክ ፖሊስ ስራ ጀመረ

አዲስ የተቋቋመው የጉሙሩክ ፖሊስ ስራ ጀመረrnrnኮንትሮባንድንና ህገ-ወጥ ንግድን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቋቋመው የጉምሩክ ፖሊስ ስራ መጀመሩ ተገለፀ፡፡rnrnኮንትሮባንድን መከላከል ዋነኛ ተግባሩ መሆኑ የተነገረው ይኸው የጉሙሩክ ፖሊስ ተጠሪነቱ ለፌዴራል ፖሊስ መሆኑም ተነግሯል፡፡rnrnበፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን  የኮንትሮባንድ ፖሊስ ዳይሬክቶሬትን ለማቋቋም የሚያስችል የስምምነት ሰነድ በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና በጉሙሩክ ኮሚሽን መካከል ተፈርሟል።rnrnበጉምሩክ የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ቀደም ሲል ሌሎች ስራዎችን ደርቦ ሲሰራ የነበረው የፀጥታ መዋቅር በአሁኑ ወቅት ኮንትሮባንድን መከላከል ዋነኛ ስራው የሆነ የጉምሩክ ፖሊስ ነው ያደራጀው፡፡rnየጉምሩክ ፖሊስ አደረጃጀቱ ተጠሪነቱ ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሆኖ ከጉምሩክ ኮሚሽን ጋር በጋራ የስራ ስምሪት የመስጠትና ስራውን በጋራ የመገምገም አሰራር ይከተላል ተብሏል፡፡rnበአሁኑ ወቅት በጥናት ላይ በመመስረት 50 በመቶ በሚሆኑት የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ላይ አዲሱ የጉምሩክ ፖሊስ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በቀሪዎቹ ኬላዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ እንደሚገባ ይጠበቃል መባሉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡rnrnየጉምሩክ ኮሚሽን ሪፎርም ከጀመረ ወዲህ 1.3 ቢሊዮን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር እንዳዋለ የሚታወስ ነው፡፡

More in Economy