Arts TVArts TV
← NewsEconomy

አቶ ወዮ ሮባ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙ

Arts TV · ኤፕሪ 8 2019

አቶ ወዮ ሮባ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሾሙrnrnአቶ ወዮ ሮባ አካኮ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸውን ኮርፖሬሽኑ አስቋል ሲል ፋና ዘግቧል።rnrnኮርፖሬሽኑን ከታህሳስ 10 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምረው ላለፉት ሦስት ወራት በተጠባባቂ ዋና ሥራ አስፈጻሚነት የመሩት አቶ ወዮ ሮባ ከመጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሹመዋል።rnrnአቶ ወዮ ወደ ስኳር ኮርፖሬሽን ከመጡበት ከ2004 ዓ.ም አንስቶ ለሰባት ዓመታት የኦፕሬሽንስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የእርሻና የፋብሪካ ኦፕሬሽን ሥራዎችን መርተዋል።rnrnወደ ኮርፖሬሽኑ ከመምጣታቸው አስቀድሞም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ማገልገላቸዉን  ሰምተናል

More in Economy