አርሲ ዩኒቨርስቲ 300 ለሚሆኑ ስደት ተመላሾች የስራ እድል እንዳመቻቸ ገለጸ ፡፡rnrnከስደት ተመላሾቹ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሰለጠኑ ሲሆን ስራ ለማስጀመርም አስፈላጊው የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡rnrnየኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮዎች ጋር በመተባበር በ11 ከተሞች በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ካሰለጠኗቸው 3500 ከስደት ተመላሽ ዜጎች 500 የሚሆኑት የአሰላ ከተማ ነዋሪዎች ሲሆኑ፤ 300 ተመራቂዎችን ማቋቋም የሚያስችል ሶስት ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ እና የስራ እድል አርሲ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተመቻችቷል፡፡rnrnየሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከሌሎች ተቋማት ጋር በመተሳሰር መስራታቸው የሚፈለገውን እድገት ለማምጣት ጉልህ ሚና እንዳለው ገልፀዋል፡፡rnrnአርሲ ዩኒቨርሲቲ ዜጎች በሀገራቸው ሰርተው እንዲለወጡ ከኢትዮጵያ ነጋዴ ሴቶች ማህበር፣ ከሲውዲን በጎ አድራጎት ድርጅት ሂውማን ብሪጅ እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከስደት ተመላሽ ዜጎችን በማቋቋም ማህበራዊ ሀላፊነቱን ለመወጣት ያከናወነውን ተግባር ሚኒስትሯ አድንቀዋል፡፡rnrnሚንስትሯ ሌሎች የትምህርት ተቋማት አርሲ ዩንቨርስቲ የጀመረውን ተሞክሮ በመውሰድ ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ጠቁመው፤ አርሲ ዩንቨርስቲን ጨምሮ ለዚህ በጎ ተግበር የተባበሩትን በሙሉ አመስግነዋል፡፡rnrnበተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሰልጥነው ወደ ስራ የሚሰማሩትን ከስደት ተመላሾች ሚኒስትሯ ባገኙት የስራ እድል ተጠቅመው ሠርተው በመለወጥ ለሌሎች አርዓያ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡rnrnየአርሲ ዩንቨርስቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዱጉማ አዱኛ በበኩላቸው ዩኒቨርስቲው ባሉት ሶስት ካንፓሶች ለተማሪዎች የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲያቀርቡ የሥራ እድል እንደተመቻቸላቸው ገልፀው፤ የልብስ እጥበት፣ የፀጉር ሥራ አገልግሎት፣ የፎቶ ኮፒና ፕሪንት ሥራ እንዲሁም የዳቦ አቅርቦት ስራ በድጋፍ በተገኘው ማሽኖች እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡rnrn






