Arts TVArts TV
← NewsSocial

ንብረትነቷ የአቢሲኒያ ፍላይት የሆነች ሲስና 172 የመማሪያ አነስተኛ አውሮፕላን በጅማ አቅራቢያ ተከስክሳ በአብራሪው ላይ ጉዳት ደረሰ

Arts TV · ሜይ 17 2019

ንብረትነቷ የአቢሲኒያ ፍላይት የሆነች ሲስና 172 የመማሪያ አነስተኛ አውሮፕላን በጅማ አቅራቢያ ተከስክሳ በአብራሪው ላይ ጉዳት ደረሰrnአውሮፕላኗ ዛሬ ጧት 4 ሰዓት ገደማ ላይ ጅማ ዞን አሰንዳቦ በተባለ አካባቢ ልምምድ ላይ እያለች የመከስከስ አደጋ ገጥሟታል፡፡rnrnበአደጋው በአብራሪው ላይ ጉዳት እንደደረሰበት የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንሙት ለማ ለኢቲቪ ገልፀዋል፡፡rnrnየአደጋውን መንስኤ ለማወቅ ተጨማሪ የማጣራት ስራ ለማከናወን የአውሮፕላን አደጋ መርማሪዎች ቡድን ወደ ስፍራው ማቅናታቸውን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡rnrn 

More in Social