ቤተ-እስራኤላውያኑ የፓርኩን ሁኔታ ለማየት ጎንደር ገብተዋልrnrnየስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ ቃጠሎ የደረሰበት ክፍል መልሶ ሊያገግም በሚችልበትና ዘላቂ ጥበቃ በሚመቻችበት መንገድ ዙሪያ ጥናት የሚያደርግ የቤተ-እስራኤላውያን ቡድን ዛሬ ረፋድ ጎንደር ገብቷል፡፡rnrnበቀድሞዋ የእስራኤል አምባሳደር በኢትዮጵያ ወይዘሮ በላይነሽ ዛባድያ የሚመራው ልዑክ በቀጣይ ወደ ተቃጠለው የፓርኩ አካባቢ በማቅናት የሚያስፈልገውን ድጋፍ ለመወሰን የሚያስችል መረጃ በአካል ይሰበስባል፤ ከሰሜን ጎንደር ዞን እና ከአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋርም ይወያያል፡፡rnrnየስሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ በመጋቢትና ሚያዝያ ወራት ባጋጠመው የእሳት ቃጠሎ አደጋ አንድ ሺህ 40 ሄክታር መውደሙ የሚታወስ ነው፡፡rnrnበተለይ ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2011ዓ.ም በነበረው ቃጠሎ በፓርኩ ከፍተኛ ውድመት መድረሱና የእስራኤል የእሳት ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች እና አንድ ሄሊኮፕተር በቦታው መሠማራታቸው የሚታወስ ነው፡፡rnrnዘገባው የአማራ መገናኛ ብዙሃን ነው፡፡






