ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከተጓጓዙ ከ29 ሚሊየን በላይ መንገደኞች 87 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር መገኘቱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።rnrn rnrnየክፍያ ጉዳናዎችን በተመለከተም የክፍያ መንገድ ኢንተርፕራይዝ ባለፉት 9 ወራት 6 ሚሊየን 38 ሺህ 800 ተሽከርካሪዎችን ምልልስ በማስተናገድ ከ191 ነጥብ 4 ሚለየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተነግሯል።rnrnየትራንስፖርት ሚኒስቴር የ9 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት እንደተገለጸው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ለተጠቃሚዎች ፈጣን አገለግሎት እንዲሰጥ እና ለጉዞም አመቺ እንዲሆን በማሰብ ባቡሮቹ በየጣቢያዎቹ የሚደርሱበትን የጊዜ ረዝማኔ ለመቀነስ ተሞክሯል።rnrnበዚህም መሰረት ከምስራቅ ወደ ምእራብ የሚጓዘውን የባቡር ጉዞ ከ15 ደቂቃ ወደ 12 ደቂቃ ዝግ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፥ ከሰሜን ወደደቡብ የሚጓዘውን የባቡር መስመር ደግሞ ከ20 ደቂቃ ወደ 15 ደቂቃ ዝቅ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።rnrnእንደሚኒስቴሩ ሪፖርት ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ባለፉት 9 ወራት በተሰራው ስራ የሀገር አቋራጭ አውቶብስ ሰምሪት መስመርን ቁጥር ወደ 223 ከፍ ማድረግ ተችሏል ነው የተባለው።rnrnየመደበኛና ወቅታዊ ከባድ የመንገድ ጥገና ስራዎችን በተመለከተም በ9 ወራት ውስጥ ከ13 ሺህ 228 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ጥገና ስራዎች መከናወናቸው ነው በሚኒስቴሩ ሪፖርት ላይ የተመለከተው ።rnrnበሀገሪቱ የነበረው የፀጥታ ችግር እና የተቋሙ የኮንትራት አስተዳደር አቅም ውስንነት ባለፉት 9 ወራት ላከናወናቸው የመንገድ ጥገና ስራዎች ስኬት እንቅፋት እንደሆኑበት ሚኒስቴሩ በሪፖርቱ አመልክቷል።
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከተጓጓዙ ከ29 ሚሊየን በላይ መንገደኞች 87 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ተገኝቷል- የትራንስፖርት ሚኒስቴር
Arts TV · ኤፕሪ 23 2019
More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019