Arts TVArts TV
← NewsSocial

በዛሬው ዕለት ትምህርት ሚኒስቴር ለሰራተኞቹ የህፃናት ማቆያ አስመረቀ

Arts TV · ሜይ 15 2019

በዛሬው ዕለት ትምህርት ሚኒስቴር ለሰራተኞቹ የህፃናት ማቆያ አስመረቀ

በዛሬው ዕለት ትምህርት ሚኒስቴር ለሰራተኞቹ የህፃናት ማቆያ አስመረቀrnየኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስትር  ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ በምረቃ ሥነ ሥርዓት ወቅት እንደተናገሩት፤ የህፃናት ማቆያው አላማ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚሰሩ ወላጆች በተለይ ሴት ሰራተኞች ከወሊድ በኋላ ወደ ሥራ ገበታቸው ሲመለሱ ልጆቻቸውን በሥራ ቦታቸው ጡት ማጥባትና በቅርበት ተከታትለው አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ እንዲችሉ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት መሆኑን ገልፀዋል።rnበማቆያው ተጠቃሚ የሚሆኑ እድሜያቸው ከስድስት ወር እስከ አራት ዓመት የሆኑ ሕፃናት እንደሆኑም ታውቋል፡፡rnበሚ/ር መ/ቤቱ የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማሰራጫ ድርጅት ከ64 ሺ ብር በላይ የሚገመት ለህፃናት ማቆያው የውጪ መጫወቻዎችን ድጋፍ ያደረገ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡rnከኢትዮጵያ ሴቶች ጤና ማህበር እና አጋርነት ለለውጥ ከተባለ የልማት አጋር ድርጅቶች ለማቆያው ምስረታ አስፈላጊ ግብዓት ለሟሟላት በግምት ብር 300 ሺ የሚጠጋ ድጋፍ ያደረጉ መሆኑ ታውቋል፡፡

More in Social