Arts TVArts TV
← NewsEconomy

በኢትዮጵያ በ8 ዓመታት ዉስጥ ከቀረጥ ነጻ ሰበብ 519 ቢሊየን ብር  ለታለመለት አላማ አልዋለም ተባለ፡፡

Arts TV · ኤፕሪ 4 2019

በኢትዮጵያ በ8 ዓመታት ዉስጥ ከቀረጥ ነጻ ሰበብ 519 ቢሊየን ብር  ለታለመለት አላማ አልዋለም ተባለ፡፡

በኢትዮጵያ በ8 ዓመታት ዉስጥ ከቀረጥ ነጻ ሰበብ 519 ቢሊየን ብር  ለታለመለት አላማ አልዋለም ተባለ፡፡rnrnከ2002 እስከ 2010 ብቻ የአገሪቱ ገንዘብ ከከረጥ ነፃ ሰበብ 519 ቢሊየን ብር ለታለመለት አላማ አለመዋሉን  የገቢዎች ሚኒስቴር ገልጿል፡፡rnrnየገቢዎች ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከሰራተኞቻቸዉ ጋር ባደረጉት ዉይይትrnrnሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከዚህ ቀደም በሌብነት መረብ የተተበተበ፤ ለማጭበርበርና ታክስ መሰወር የሚያግዙና ዉስብስብ የሆኑ ህጎችና የስራ መመሪያዎች የነበሩበት፤ ወቅቱና ቦታዉ የሚፈልገዉ የሰዉ ሃይል በሚመጥነዉ ቦታ ያልተመደበበት፤ ከግዜ ወደ ግዜ ገቢዉ እያሽቆለቆለ የነበረበትና የንግዱ ማህበረሰብ የቅሬታ ቋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡rnበአገሪቱ የኮንትሮባንድ ዝዉዉር ከፍተኛ ሆኖ ሳለ 55 ኬላዎች ብቻ እንዲኖሩ መደረጉና ኬላዎቹም ያሉበት ስፍራ ከፍተኛ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ባለበት ቦታ አለመሆኑ መስሪያ ቤቱ የነበረበት ችግር መሆኑ ተነስቷል፡፡rnከሪፎርሙ ወዲህ ግን ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያስፈልገዉ የሰዉ ሃይል በብቃትና በዉጤታመነት በመመደቡ በስራ ስኬት እየተመዘገበ ነዉ ተብሏል፡፡rnrnያለአግባብ ከቀረጥ ነፃ በሚል ከታለመለት አላማ ዉጪ እንዲዉል ሲደረግ ከነበሩት ስራዎች ዉስጥ በፍርድ ቤት በመክሰስ 1.5 ቢሊየን ለመንግስት ገቢ እንዲደረግ መደረጉ ፤ከዉዝፍ እዳ 14 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉና ከአምናዉ ጋር ሲነፃፀር ሲያሽቆለቁል የነበረዉ ገቢ በ12በመቶ እድገት ማሳየቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሪፎርሙ እያመጣ ያለዉ ለዉጥ ተጨባጭ ማሳያ መሆኑ ተነስቷል፡፡rnrnየሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን አሰራር ቆልፈዉ የያዙና ለሌብነት በር የሚከፍቱ ከ34 በላይ ህጎች እየተሻሻሉ መሆናቸዉና 1.3 ቢሊየን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ እቃ መያዙ ህገወጥነት ሊቀጥል እንደማይችል ማሳያ መሆኑ በዉይይቱ ተነስቷል፡፡rnመስፈርት ሳያሟሉ ለቦታዉ የሚያስፈልግ የትምህርትና የስራ ልምድ ሳይኖራቸዉ ከመከላከያ በየኬላዎች ተመድበዉ ይሰሩ የነበሩ 108 ሰዎች በአመራሩ ዉሳኔ እንዲነሱ ተደርጎ፤ በቂ የስራ ልምድና እዉቀት ባላቸዉ ሰዎች መተካታቸዉ፤ የኬላዎቹ ቁጥር ላይ 39 አዳዲስ ኬላዎችን በመጨመር 94 እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል ተብሏል፡፡rnrn 

More in Economy