Arts TVArts TV
← NewsPolitics

በአሜሪካ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስተዋወቅ ያለመ የውይይት መድረክ ሊካሄድ ነዉ፡፡

Arts TV · ሜይ 10 2019

በአሜሪካ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስተዋወቅ ያለመ የውይይት መድረክ ሊካሄድ ነዉ፡፡

በአሜሪካ በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስተዋወቅ ያለመ የውይይት መድረክ ሊካሄድ ነዉ፡፡rnrnየውይይት መድረኩ  ግንቦት 7 እና 8 ቀን 2011 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ ነዉ የሚካሄደዉ፡፡rnrnየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት፣ የንግድ ስራና ሌሎች የትብብር እድሎችን ለማስተዋወቅ ያለመ የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት ማቀዱን የዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት ገልጿል።rnrnውይይቱ አሜሪካዊያን በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ በኢትዮጵያ የእድገት እና የንግድ ለውጥ አስተዋፅኦ ለማበርከት ያለመ መሆኑን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በድረ-ገፁ ይፋ ባደረገው መግለጫ አስታውቋል።rnrnበውይይቱ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የንግድ ሥራ መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ ዋና ዋና የአሜሪካ ኩባንያዎች፣ በበጎ አድራጎት ስራ ላይ የተሰማሩ እና የሁለቱን አገሮችን የንግድ እና የኢኮኖሚ ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት ያላቸው አካላት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

More in Politics