Arts TVArts TV
← NewsPolitics

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች የከንቲባውን ቢሮ አቃጠሉ፡፡

Arts TV · ኖቬም 26 2019

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች የከንቲባውን ቢሮ አቃጠሉ፡፡

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች የከንቲባውን ቢሮ አቃጠሉ፡፡rnrnተቃዋሚዎቹ በምስራቃዊ የኮንጎ ግዛት በምትገኘው ቤኒ ከተማ በደረሰ ጥቃት 8 ሰዎች በመገደላቸው ተበሳጭተው ነው ይህን ድርጊት የፈፀሙት ተብሏል፡፡rnrnነዋሪዎቹ በተደጋጋሚ መንግስት ከሚደርስባቸው ጥቃት እንዲታደጋቸው ቢወተውቱም አሁንም ከመንግስ በኩል የህይዎት ዋስትና እንደሌላቸው ነው የሚናገሩት፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ጥቃቱን ያደረሱት በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው አላይድ ዲሞክራቲክ ፎርስ የተባለው ተቃዋሚ ቡድን አባላት ሊሆኑ እንደሚችሉ ጥርጣሬ አለ፡፡rnrnአላይድ ዲሞክራቲክ ፎርስ የተባለው ተቃዋሚ ሀይል በኡጋንዳ ድንበር አካባቢ በመትገኘው በማእድን በበለፀገችው ቤኒ ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ሀይሎች መካከል ዋነኛው መሆኑ ይነገራል፡፡rnrnባለፈው ወር ብቻ በዚህ አካባቢ ከ70 በላይ ንፁሀን ዜጎች ተገድለዋል ነው የተባለው፡፡rnrnበዚህ ብስጭት የገባቸው ነዋሪዎች የተባበሩት መንግስታት ቢሮ አካባቢ በመሰባሰብ ተቃውሟቸውን ከመግለፅ አልፈው የከንቲባውን ቢሮ እስከማቃጠል ደርሰዋል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Politics