ደቡብ ሱዳን አሜሪካ እንድትታገሳት የተማፅኖ ጥያቄ አቀረበች፡፡rnrnየደቡብ ሱዳን መንግስት ዋነኛ ደጋፊ የሆነችው ዋሽንግተን ደቡብ ሱዳናዊያን ተቀናቃኝ ሀይሎች የአንድነት መንገግስት ለመመስረት ዳተኝነት አሳይተዋል በሚል ቅሬታዋን መግለጿን ተከትሎ ነው ጁባ አቤቱታውን ያቀረበችው፡፡rnrnሁለቱ ወገኖች የጥምር መንግስት ለመመስረት ይዘውት የነበረውን ቀጠሮ ለተጨማሪ 100 ቀናት በማራዘማቸው ቅር የተሰኘችው አሜሪካ ከደቡብ ሱዳን ጋር ያለኝን ግንኙነት ዳግም መፈተሸ አለብኝ የሚል አቋም ላይ ደርሳለች ነው የተባለው፡፡rnrnየደበብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና አለም አቀፍ ትብብር ቃል አቀባይ <strong>ማዌን ማኮል</strong> አሜሪካ የሰላም ሂደቱን መደገፏን እንዳታቆም ስንጠይቅ እኛም የአሁኑ ቀጠሯችን የመጨረሻው እንደሚሆን ተስፋ በማድረግ ነው ብለዋል፡፡rnrnዘ ኢስት አፍሪካን እንደዘገበው የጥምር መንግስት ምሰረታው የተራዘመው የተቃዋሚ መሪው ሪክ ማቻር ገና ያልተጠናቀቁ ጉዳዮች ስላሉን እነሱን ስንጨርስ ሁሉም ነገር ይደርሳል የሚል ሀሳብ በማቅረባቸው ነው፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ





