የዚምባቡዌ ዶክተሮች የማህበራቸውን መሪ መታገት ለመቃወም የስራ ማቆም አድማ መትተዋል፡፡rnrnሀራሬ የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ የህክምና ባለ ሞያዎች ፒተር ከሌለ ስራ የለም የሚል መፈክር ይዘው ነው ለተቃውሞ አደባባይ የወጡት፡፡rnrnቢቢሲ እንደዘገበው ሰልፈኞቹ የዚምባቡዌ የሀኪሞች ማህበር መሪ የነበሩት ዶክተር ፒተር ማጎምቤይ ሰሞኑን ታግተው ተወስደዋል የሚል እምነት አላቸው፡፡rnrnዶክተሩ ባለፈው ቅዳሜ እለት በዋትስ አፕ በላኩት መልእክት በማያውቋቸው ሶስት ግለሰቦች ታፍነው መወሰዳቸውን አመላክተው ከዚያን ወዲህ ድምጻቸው አልተሰማም፡፡rnrnየተቃዋሚ መሪው ኔልሰን ቻሚሳ በቲውተር ገፃቸው ላይ በሰፈሩት ፅሁፍ በሰማሁት ነገር ልቤ በሀዘን ተሰብሯል ብለዋል፡፡rnrnዶክተር ፒተር በቅርብ ሳምንታት ለሀኪሞች የደመወዝ መጠን እንዲሻሻል መንግስት ላይ ጫና ለማሰሳደር ተከታታይ ሰላማዊ ሰልፎችን ሲያዘጋጁ ነበር ተብሏል፡፡rnrnየዚምባቡዌ መንግስት ቃል አቀባይ ኒክ ማንግዋና የሀኪሞቹን ጥርጣሬ መሰረተ ቢስ ነው መንግስት ዜጎቹን የሚያግትበት ምንም ዓይነት ምክንያት የለውም ሲሉ ሁኔታውን አስተባብለዋል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ





