<strong>በቅርቡ የተቋቋመው የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ለግጭቶች ዋነኛ መንስኤዎችን በማጥናት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እሰራለሁ አለ ፡፡</strong>rnrnኮሚሽኑ በቀጣይ ጊዜያት እውነትና ፍትህ ላይ መሰረት ያደረገ እርቅ ለማውረድ እንደሚሰራም ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡rnrnኮሚሽኑ ወደ ስራ የገባው በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ማህበረሰባዊና ፖለቲካዊ ምክንያት በህዝቦች መካከል የተደራረቡ የቁርሾ ስሜቶችን ለማከም እውነተኛና ፍትህን መሰረት ያደረገ እርቅ ማውረድ አስፈለጊ መሆኑን አምኖ ነበር ተብሏል፡፡rnrnየእርቅ ሰላም ኮሚሽኑ በአዋጅ ከተሰጡት ስልጣንና ተግባራት በመነሳት በቀጣይ በግጭቶቹ መንስኤዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚንቀሳቀስም ተነግሯል፡፡rnrnየእርቅ ሰላም ኮሚሽኑ ሰብሰቢ ብርሃን እየሱስ፣ የእርቅ ሂደቱ በባለሙያዎች የግጭቶችን ምንጭ በማጥናት ይቅር በማባባል በውይይት ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የሚሰራ ነው ብለዋል፡፡rnrnየሚቀርቡ አቤቱታዎችንም በባለሙያዎች ምርምራ በማድረግ የቅሬታዎችን መንስኤዎች በመመርመር ዘላቂ ሰላምና እውነተኛ ፍትህ እንዲሰፍን ጥረት እንደሚደረግም በመግለጫው ተነግሯል፡፡ Picture @FBC
← NewsSocial
በቅርቡ የተቋቋመው የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ለግጭቶች ዋነኛ መንስኤዎችን በማጥናት ዘላቂ ሰላም ለማምጣት እሰራለሁ አለ
Arts TV · ኤፕሪ 30 2019





