Arts TVArts TV
← NewsSocial

በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ተከስቶ በነበረው ግጭት የተቃጠሉ ቤቶች መልሰው እየተሰሩ ነው።

Arts TV · ሜይ 17 2019

በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ተከስቶ በነበረው ግጭት የተቃጠሉ ቤቶች መልሰው እየተሰሩ ነው።

በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ዞኖች ተከስቶ በነበረው ግጭት የተቃጠሉ ቤቶች መልሰው እየተሰሩ ነው።rnrnበአሁኑ ሰአት 6 ሺህ 652 ቤቶችን ለመገንባት ጥረት እየተደረገ ሲሆን፥ እስከአሁን ከ1 ሺህ በላይ ቤቶች ቆርቆሮ ለብሰዋል።rnrnየአማራ ክልል አደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራምና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አማረ ክንዴ እንደገለፁት፥ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ጉንትር በተባለው ቀበሌ ብቻ ከሚገነቡት 507 ቤቶች 432ቱ ቆርቆሮ የማልበስ ስራ ተከናውኗል።rnrnበዞኑ 36 ሺህ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የተመለሱ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ አማረ፥ በዘላቂነት ለማቋቋም ድጋፉ እንደቀጠለ ነው ብለዋል።rnrnከዚህ በተጨማሪም ጊዜያዊ ድጋፎች እየተደረጉ ሲሆን፥ ለአርሶ አደሩ የእርሻ ስራና ለክረምት ምግብ የሚሆን አቅርቦት ለማድረግም ዝግጅቱ ተጠናቋል።rnrnበክልሉ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ቃል ከተገባው 720 ሚሊየን ብር 318 ነጥብ 6 ሚሊየኑ ገቢ የተደረገ ሲሆን፥ ይህንን ገንዘብ በፍትሀዊነት ለታለመለት አላማ ለማዋል በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

More in Social