Arts TVArts TV
← NewsSocial

በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች በአሁኑ ወቅት ፈተና መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ተናገሩ፡፡

Arts TV · ሜይ 2 2019

በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች በአሁኑ ወቅት ፈተና መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ተናገሩ፡፡

በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች በአሁኑ ወቅት ፈተና መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ተናገሩ፡፡rnrnፕሬዝዳንቷ ይህንን የተናገሩት የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በኢትዮጵያ  እየተከበረ ባለበት ወቅት ነዉ፡፡rnrnከረቡዕ  ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበር የጀመረው 26ኛውን አለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ቀን፥ በዛሬው እለትም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በሚካሄድ ውይይት ቀጥሎ ውሏል።rnrnበአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው መርሃ ግብር ላይም መገናኛ ብዙሃን በነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲሁም በዴሞክራሲያ ስርዓት ግንባታ ላይ ባላቸው ሚና ላይ ትኩረት በማድረግ ነው እየመከረ ነዉ፡፡rnrnበአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀን ላይም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባደረጉት ንግግርም በኢትዮጵያ ከፍተኛ ለውጥ እየተካሄደ መሆኑን በመጥቀስ፤ ለውጡም ለሚዲያው ነፃነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልፀዋል።rnrnኢትዮጵያም  በቀጣይ ዓመት ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ መሆንዋንም ተናግረዋል፡፡rnrnበማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች በአሁኑ ወቅት ፈተና መሆናቸውን ያነሱት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፤ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ተሳታፊዎች በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፆች የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎችን እንዴት መከላከል ይቻላል የሚለው ላይ ትኩረት አደርገው እንዲመክሩ እና እንዲሰሩም ጠይቀዋል።rnrn 

More in Social