Arts TVArts TV
← NewsAfrica

ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለሩሲያ የጦር ሰፈር ልትፈቅድ ነው

Arts TV · ጃን 11 2019

<strong>ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለሩሲያ የጦር ሰፈር ልትፈቅድ ነው</strong>rnrnየማዕከላዊ አፍሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ሜሪ ኖኤል ኮዬራ ሩሲያ በሀገራችን  የጦር ሰፈር ለመገንባት ያቀረበችውን ጥያቄ በመልካም ጎኑ ነው የምናየው ብለዋል፡፡rnrnፕሬስ ቴሌቭዥን እንደዘገበው ሩሲያ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወታደሮችን ለማሰልጠን ሙያተኞቿን ስትልክ በመርህ ደረጃ በሀገሪቱ የጦር ሰፈር ለመገንባት የሚያስችላትን ስምምነት አድርጋለች ፡፡rnrnእስካሁን ዝርዝር ሁኔታዎች ላይ ባንወያይም ወደፊት የሁለቱም ሀገራት ባለ ስልጣናት ተገናኝተው ለመመካከር ዝግጁ ናቸው ነው ያሉት የመከላከያ ሚኒስትሯ ፡፡rnrnመከላከያ ሚኒስትሯ እንዳሉት የአፍሪካ ህብረትም ሂደቱን ለማገዝ ፍላጎት ስላለው ከባለስልጣናቱ ጋር የሚወያይበት ሁኔታ ይመቻቻል፡፡rnrnሩሲያ እና ቻይና በአፍሪካ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በዓይነ ቁራኛ የምትከታተለው አሜሪካ ግን   ነገሩን አፍሪካዊያንን በመደለል የሚደረግ ሸፍጥ ስትል አጣጥላዋለች፡፡rnrnየአሜሪካ የደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን ሩሲያ እና ቻይና አፍሪካ ውስጥ ስግብግብነት እያጠቃቸው ነው በማለት ነው ትችታቸውን የሰነዘሩት፡፡rnrnየሀገሪቱ ባለስልጣናት በበኩላቸው ህዝባቸው በሩሲያ ላይ እምነት ስላለው በጋራ መስራታቸው ወደፊት መልካም አጋጣሚዎች  ይፈጠራሉ  የሚል ተስፋ እንዳላቸው  ተናግረዋል፡፡

More in Africa