Arts TVArts TV
← NewsAfrica

ፖፕ ፍራንሲስ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀመሩ፡፡

Arts TV · ሴፕቴ 5 2019

ፖፕ ፍራንሲስ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀመሩ፡፡

ፖፕ ፍራንሲስ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀመሩ፡፡rnrnሶስት ሀገራትን የመጎብኘት መርሀ ግብር ተይዞላቸው ወደ  አፍሪካ የመጡት ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ የመጀመሪያ መዳረሻቸውን ሞዛምቢክ አድርገዋል፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ፖፑ ድህነት፣ የእርስ በርስ ግጭት እና የተፈጥሮ አደጋዎች የሚበዛባቸው ሶስት የአፍሪካ ሀገራትን ለመጎብኘት ነው ጉዟቸውን የጀመሩት፡፡rnrnበዚህም መሰረት የሞዛምቢክ ቆይታቸውን እንዳጠናቀቁ ቀጣዩ ጉዟቸው ወደ ማዳጋስካር እና ሞሪሺየስ ይሆናል ነው የተባለው፡፡rnrnፖፕ ፍራንሲስ ለጉዞ ከመነሳታቸው  አስቀድሞ ባስተለፉት መልእክት መላው አፍሪካዊያን በእርቅ እና በወንድማማችነት መንፈስ እንዲተባበሩ እና ሰላምን እንዲያሰፍኑ አደራ ብለዋል፡፡rnrnበተለይ በሞዛምቢክ ያለው የሰላም እጦት እና በተደጋጋሚ በአውሎ ንፋስ አደጋ መመታት እንዳሳዘናቸውም ተናግረዋል፡፡rnrnሞዛምቢክ ሲገቡ በደማቅ ወታደራዊ ሰልፍ እና በባህላዊ የሙዚቃ እና የዳንስ ትርዒት የታጀበ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡rnrnበሶስቱም ሀገራት በሚያደርጓቸው ጉብኝቶች ከየ ሀገራቱ ባለ ስልጣናት ጋር ስለ ሰላም እና ስለ አንድነት በሰፊው ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Africa