ኢትዮጵያ እና ኬንያ ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸውን ይበልጥ ማጠናከር አለባቸው ሲሉ የኬንያዉ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ገልጸዋል።rnrnበኬንያ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉስልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ትናንት ከኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ጋር የሁለቱን አገሮች የኢኮኖሚ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ዙረያ ተወያይተዋል።rnrnበነበረው ውይይት ሁለቱ አገሮች ረጅም ዘመን ያስቆጠረ የህዝበ ለህዝብ ግንኙነታቸውን እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም የኢኮኖሚ ትስስሩን ማሳደግ አለባቸው ሲሉ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።rnrnበሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ትስስር ማዘመንና ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ነው ዶ/ር ዊለያም ሩቶ የገለጹት፡፡rnrnየ ውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ሁለቱ አገሮች በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በተለይም በቆዳ ኢንዱስትሪ በትብብር በመስራት ለዜጎች የስራ እድል መፍጠርና ኢኮኖሚውን የማሳደግ ስራ ላይ አትኩረው እንደሚሰሩ በነበረው ውይይት መግባባት ላይ ደርሰዋል።
← NewsAfrica
ኢትዮጵያ እና ኬንያ ኢኮኖሚያዊ ትስስራቸውን ይበልጥ ማጠናከር አለባቸው ሲሉ የኬንያዉ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዊሊያም ሩቶ ገልጸዋል።
Arts TV · ሜይ 1 2019






