በኡጋንዳ ከፍተኛ የኢቦላ ወረርሽኝ ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት መኖሩ ተገለፀ፡፡rnrnየኢቦላ ወረርሽኝ ከተቀሰቀሰባት ኮንጎ ህገወጥ ስደተኞች ወደ ሀገሪቱ እየፈለሱ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ነው የቫይረሱ ስርጭት ስጋት የሆነው፡፡rnrnበዲሞክራቲክ ኮንጎ ከወራት በፊት በተቀሰቀሰው ግጭት የተነሳ ከ60 ሺህ በላይ የሚሆኑ የሀገሪቱ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡rnrnከተፈናቃዮቹ ጥቂቶቹ በኡጋንዳ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የገቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ወደ ድንበር ከመድረሳቸው በፊት በወታደሮች ተይዘው የኢቦላ ቫይረስ ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡rnrnየኡጋንዳ መንግስት ምንጊዜም ስደተኞችን ለመቀበል በራችን ክፍት ነው ያለ ሲሆን፤ አሁንም ስደተኞችን መቀበላችንን እንቀጥላለን ፤ነገርግን የሀገራችንን ዜጎች ጤና ስጋት ላይ የሚጥል እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ እንወስዳለን ብሏል፡፡rnrnጥቂት የማይባሉ ተፈናቃዮች በህገ ወጥ መንገድ የኡጋንዳን ድንበር ጥሰው እየገቡ በመሆኑ የቫይረስ ስርጭት ይከሰታል የሚለው ስጋት እያየለ መጥቷል፡፡rnrnዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ጉዳዩ እንዳሳሰባቸውና ለስደተኞቹ አስፈላጊውን ህክምናና እርዳታ ለማቅረብ መቸገራቸውን የገለጹ ሲሆን ጾታዊ ጥቃቶች ሊከሰቱ ይችላል የሚል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡rnrnበኮንጎ የኢቦላ ቫይረስ ከተቀሰቀሰበት ከፈረንጆቹ 2018 አንስቶ ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን ከ9መቶ በላይ የሚሆኑ መሞታቸው ይታወሳል፡፡rnrn.






