በታንዛኒያ የነዳጅ ጫኝ ቦቴ ላይ በደረሰው ቃጠሎ የሟቾች ቁጥር ጨምሯል፡፡rnrnየንግድ ማእከል በሆነችው ሞሮጎሮ ከተማ አቅራቢያ አንድ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቴ ተገልብጦ ነው ቀጣሎወ የተቀሰቀሰው፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ቦቴው ሲገለበጥ የሚፈሰውን ነዳጅ ለመቅዳት በሚሻሙ ሰዎች ላይ የደረሰው አደጋ በርካቶችንም አቁስሏል ነው የተባለው፡፡rnrnበወቅቱ አሽከርካሪው መኪናው እንደደተገለበጠ እሳት እንደሚነሳ በመገመት ሰዎች ከአካባው እንዲርቁ ቢያስጠነቀቅም ሰሚ አላገገኘም ነበር ተብሏል፡፡rnrnየሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ቃጠሎው የተቀሰቀሰው አደጋው እንደደረሰ አንድ ግለሰብ የመኪናውን ባትሪ ፈትቶ ለመውሰድ ሲሞክር እንደሆነ ደርሰንበታል ብለዋል ፡፡rnrnበሆስፒታል የህክምና ክትትል የሚደረግላቸውን የአደጋው ተጠቂዎች ለማዳን ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ አንደሆነ የዳሬሰላም ሆስፒታል ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ






