Arts TVArts TV
← NewsSocial

መንግሥት የሚደጉመው የፓልም ዘይት የጤናችግር  ስለሚያመጣ በሌሎች ፈሳሽ ዘይቶች እንዲቀየር ጤና ሚኒስቴር ጠየቀ

Arts TV · ኤፕሪ 30 2019

መንግሥት የሚደጉመው የፓልም ዘይት የጤናችግር  ስለሚያመጣ በሌሎች ፈሳሽ ዘይቶች እንዲቀየር ጤና ሚኒስቴር ጠየቀ።rnrnከፍተኛ የጤና ችግር ያመጣል የተባለው የፓልም ዘይት ከ90 እስከ 95 በመቶ በድጎማ የሚገባ ሲሆን፣ ይህንን ለመቀየር መጠየቁን ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያስታወቀው፡፡rnrnሚኒስቴሩ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የመድኃኒትና ምግብ ቁጥጥር ባለሥልጣን ያቀረባቸውን ጥናቶች ምክረ ሐሳብ መሠረት በማድረግ፣ የፓልም ዘይት በፈሳሽ ዘይቶች እንዲቀየር ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ማሳወቁን ተናግሯል፡፡rnrnለንግድ ሚኒስቴር የተላከው ደብዳቤ እንደሚለው፣ ጤና ሚኒስቴር በገበያ ላይ ያሉ የምግብ ዘይቶች በጤና ላይ ችግር እየፈጠሩ ነው የሚል ምክረ ሐሳብ አቅርቧል፡፡rnrnበአሁኑ ጊዜ እየቀረበ ያለው የፓልም ዘይት ለጤና ተመራጭ ስላልሆነ ደረጃ በደረጃ በሌሎች ለጤና ተስማሚና ተመጣጣኝ ዋጋ ባላቸው ፈሳሽ ዘይቶች (በሱፍ፣ በአኩሪ አተር፣ በሰሊጥ፣ በኑግና በሌሎች) እንዲተኩ ነው ሐሳብ የቀረበው፡፡rnrnሪፖርተር እንዳስነበበው ጤና ሚኒስቴር ይህን ችግር ለመቅረፍ የፓልም ዘይትን በሌሎች ፈሳሽ ዘይቶች መተካት አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሶ በጠየቀው መሠረት፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ንግድ ሚኒስቴር ጉዳዩን ገምግሞ የውሳኔ ሐሳብ ለጠቅላይ ሚኒስትር በጽሕፈት ቤት በአጭር ጊዜ እንዲያቀርብ ውሳኔ ተላልፏል፡፡rnrnበዓለም አቀፍ ደረጃ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ሲሆን፣ በኢትዮጵያም ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ጫና ተላላፊ ከሆኑት ጋር እኩል የሰውን ጤና የሚገዳደሩ እየሆኑ መጥተዋል፡፡rnrnተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች ቀዳሚ መነሻ  የአመጋገብ ሥርዓትና የአኗኗር ዘይቤ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥም የምግብ ዘይት አጠቃቀም ተጠቃሽ ነው፡፡

More in Social