Arts TVArts TV
← NewsSocial

ሁለተኛው ኢትዮ ኪድስ የልጆች አዉደ ርዕይ በመኮንኖች ክበብ ተካሄደ፡፡

Arts TV · ሜይ 20 2019

ሁለተኛው ኢትዮ ኪድስ የልጆች አዉደ ርዕይ በመኮንኖች ክበብ ተካሄደ፡፡

ሁለተኛው ኢትዮ ኪድስ የልጆች አዉደ ርዕይ በመኮንኖች ክበብ ተካሄደ፡፡rnrnለህጻናትና ታዳጊዎች የሚሆኑ ምርትና አገልግሎቶች ብቻ የቀረቡበትን አዉደ ርዕይ   በርካታ ህጻናት ከወላጆቻቸው ጋር በመሆን ጎብኝተውታል፡፡rnrnለህጻናትና ታዳጊዎች ታስቦ የተዘጋጀዉ አዉደ ርዕይ በመሆኑ የተለያዩ የህጻናት አልባሳት፣ መጻህፍት፣ ሲዲዎችና ዲቪዲ እንዲሁም የመጫወቻ ቁሳቁሶች በስፋት የቀረቡበት ነበር፡፡rnrnበተጨማሪም አውደ ርዕዩን ለሚጎበኙ ህጻናት የተለያዩ የመዝናኛ አማራጮችም የቀረቡ ሲሆን የተለያዩ የህጻናት መጫወቻዎች እንዲሁም የሰርከስ ትርኢት እና የህጻናት ሙዚቃዎች  ቀርበዋል፡፡rnrnበአውደ ርዕዩ ከህጻናት ጋር የተያያዙ ምርትና አገልግሎቶች ያሏቸው አምራቾች ፣አከፋፋዮች እና በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች የተሳተፉ ሲሆን ፤በህጻናት ልዩ ቁጠባ ላይ የተሰማሩ ባንኮችና የመድህን ድርጅቶች አገልግሎታቸውን አስተዋውቀዋል፡፡rnrnከህጻናት ጋር የተያያዙ ስራዎችን የሚሰሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የሚሰጡዋቸውን አገልግሎች አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የማስተዋወቅ ስራ ሰርተዋል፡፡rnrnኢትዮ ኪድስ የልጆች አውደ ርዕይ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በመሆን እየተዝናኑ የተለያዩ ምርቶችን በአንድ ቦታ የሚሸምቱበትና ድርጅቶችም በህጻናት ዙሪያ የሚሰጧቸውን አገልግሎቶች ለማስተዋወቅ ሰፊ እድል እንዲያገኙ  የታለመ መሆኑን አዘጋጆቹ ነግረውናል፡፡rnrn rnrn 

More in Social